2ኛ ትምህርት: ወልድ

EAQ314_02

ሰኔ 28 – ሐምሌ 4, 2ዐዐ6 ዓ.ም

ሰንበት ከሰዓት

ለዚህ ሳምንት የሚከተሉትን ጥቅሶች ያንብቡ፤ ማቴ. 24፡3ዐ ፣ ዳን 7፡13፣14፣ ማቴ. 11፡27 ፣
ሉቃ. 5፡17-26፣ ዮሐ. 8፡58፣ ማቴ. 2ዐ፣28፡፡

የመታሰብያ ጥቅስ፡- “እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም” ማር. 10፡45፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ዓመት ህዝብን ካገለገለ በኋላ፤ ደቀመዛሙርቱን “ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደሆነ ይሉታል? (ማቴ. 16፡3) ብሎ ጠየቀ፡፡ ሰዎች ስለክርስቶስ የሚሉትን መናገር አስቸጋሪ አልነበረም፡፡ አስቸጋሪ የነበረው ግን “እናንተስ እኔን ማን ነው ትሉኛላችሁ” (ማቴ. 16፡15) የሚለው የክርስቶስ ቀጣዩ ጥያቄ ነበር፡፡ ክርስቶስ የጠየቀው ውጫዊ ገጽታውን ባህርዩን በተመለከተ ያላቸውን አስተያየት ሳይሆን ማንነቱን ነበር፡፡ ይህም ጥያቄ የደቀመዛሙርቱን ግላዊ እምነትና መረዳት የሚጠይቅ ነበር፡፡ ቢፈጥንም ሆነ ቢዘገይ ሁሉም ሰው ይህንን ጥያቄ ሊመልስ ግድ ነው፡፡ እያንዳንዱ በግሉ ክርስቶስ ማን እንደሆነ ይወስናል፡፡ ሌሎች የሚሉትን ሰምቶ መድገም ወይም ሌሎች ስላመኑ ማመን አይደለም መልሱ በታማኝነት የራሳችን እምነት ሊሆን ይገባል፡፡ እናም
የእያንዳንዱ ሰው መዳረሻ በዚህ ጥያቄ ምላሽ ላይ ይወሰናል፡፡

በዚህ ሳምንት ክርስቶስ ራሱ በተናገራቸውና በሠራቸው ሥራዎች ውስጥ የዚህን ጥያቄ ምላሽ እንፈልጋለን፡፡ ዓላማችንም በእምነት ልክ ጴጥሮስ እንዳለው “አንተ ክርስቶስ የህያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” የሚል ምላሽ ይሆናል፡፡? (ቁ. 16)

ለሐምሌ 5 2006 ሰንበት የዚህን ሳምንት ትምህርት አንብበው ይዘጋጁ፡፡

እሁድ  ሰኔ 29 2ዐዐ6 ዓ.ም

የሰው ልጅ

“የሰው ልጅ” የሚለው ይህ መጠሪያ በተለምዶ ጌታችን ኢየሱስ ራሱን የሚወክልበት ነበር፡፡ ክርስቶስ ራሱን ከ8 ጊዜ በላይ የሰው ልጅ በማለት ተናግሯል፡፡ ሌሎች ሰዎች በዚህ ስም በፍጹም አልጠሩትም፡፡ እርሱ ራሱን በዚህ ስም ይጠራ የነበረው በአእምሮው ዓላማ ስለነበረው ነው፡፡
ይህ ዓይነት ዘይቤያዊ አገለላለጽ በብሉይ ኪዳን ዘመን የተለመደ ነበር፡፡ በአንድ ሥፍራ ብቻ ሰብዓዊነቱን ለመግለጽ ከተጠቀመው ሌላ በሁሉም ሥፍራ ራሱን የሰው ልጅ በሚል ስያሜ ተጠቅሟል፡፡
ቅዱሳት መጻህፍት ክርስቶስን እውነተኛ የሰው ልጅ መሆኑን ያሳያሉ፡፡ ልጅ እንደሚወለድ ተወለደ፣ እንደ ልጅ አደገ (በጥበብና በቁመት ያድግ ነበር) (ሉቃስ 2፡4ዐ፣52) ወንድሞችና እህቶች ነበሩት (ማቴ. 13፡55፡56) ምግብ በልቷል (ማቴ. 9፡11)፣ እንቅልፉን ተኝቷል (ሉቃስ 8፡23)፣ ይደክመው ነበር፡፡ (ዮሐ. 4፡6)፣ በረሃብና በውኃ ጥማት ተሠቃይቷል (ማቴ. 4፡2፣ ዮሐ. 19፣28)፡፡ ኃዘንና ጭንቀትንም ተለማምዷል (ማቴ. 26፡37)፡፡

በሥጋዊ ዓይን ለተመለከተው ክርስቶስ በብዙ ህዝቦች መካከል እንደኖረ አንድ ተራ ሰው ነበር፡፡ በእርሱ ዘመን የነበሩ ሰዎችም ከማንኛውም ሰው የተለየና የሚበልጥ ነገር አላዩበትም (ማቴ. 7፡46) ሰዎችም ልክ ከእነርሱ እንደ አንዱ ነበር ያስተናግዱት የነበረው በእርሱም ስቀውበታል (ሉቃስ 8፡35)፣ ንቀውታል ወይም ተችተውታል (ሉቃስ 22፡63)፡፡ ለእነርሱ እንደማንኛውም ሌላ ሰብዓዊ ሰው ነበር፡፡

እንደ አለመታደል ሆኖ በዚህ መጠሪያ ውስጥ ሊታይ የሚገባውን ታላቅ ነገር ማየት አቃታቸው እንደ ዳንኤል 7፡13-14 አገላለጽ “የሰውን ልጅ የሚመስል በሰማይ ደመና መጣ ‘በዘመኑም ወዳረጀው አቀረቡት’ መንግሥትም፣ ክብርም፣ ስልጣንም ግዛትም ተሰጠው፡፡ አይሁዳውያን ይህንን የሰው ልጅ በመሲህ መስለውታል፡፡ የሱስ ይህንን ስም (መጠሪያ) ሲጠቀም በግማሽ በተሸፈነ (በተደበቀ) መልኩም ቢሆን እርሱ ተስፋ የተደረገው መሲህ ሥጋ የለበሰው ክርስቶስ መሆኑን እየገለጸላቸው ነበር፡፡

ማቴ. 24፡3ዐ፣25፣ 26፡64ን ያንብቡ፡፡ በነዚህ ቁጥሮች ካሉት የክርስቶስ ቃላት የትኞቹ ዋና ነጥቦች ናቸው ዳን. 7፡13,14ን የሚያስታውሱን?

_____________________________________________________________
_____________________________________________________________

ክርስቶስ ሙሉ በሙሉ ሰው መሆኑን ማወቅ ለእኛ በጣም አስፈላጊ የሚሆነው ለምንድነው? በመዳናችን ውስጥ የእርሱ ሰው መሆን የሚሠጠን ትልቅ ትርጉም ምንድነው? በየዕለቱ ባለን የህይወት ትግል ውስጥ የእርሱ ሰው መሆን የሚሠጠን ትርጉም ምንድነው?

_____________________________________________________________
_____________________________________________________________

ሰኞ  ሰኔ 3ዐ, 2006 ዓ.ም

የእግዚአብሔር ልጅ

የእግዚአብሔር ልጅ የሚለው መጠሪያ በገብርኤል ብቻ ሳይሆን (ሉቃስ 1፡35) ሌሎችም ብዙዎች ክርስቶስን ለመጥራት የፈለጉ ሰዎች ተጠቅመውበታል፡፡ (ማቴ. 14፡33፣ ማር. 15፣39፣ ዮሐ. 1፡49፣ 11፡27)፡፡ ይህን ስም ክርስቶስ ራሱ የተቀበለው ቢሆንም አይሁዶች ይህንን ከሰሙ በድንጋይ ወግረው ስለሚገድሉት በጣም በጥንቃቄ ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በተለያዩ ብዙ መንገዶች እርሱ ከአባቱ ጋር ያለውን አንድነት ገልጿል፡፡

በጥምቀቱ ጊዜ እግዚአብሔር አብ ክርስቶስ ልጁ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡ (ማቴ. 3፡17) በመለወጥ ተራራ ላይም በተመሳሳይ መልኩ አሳይቷል (ማቴ. 17፡5)

የእነርሱ የአባትነትና የልጅነት ግኑኝነታቸው ንፅፅር በሌላው ሁኔታ የተለየ ነበር በዓለማት መካከል ይህንን የመሰለ ቅርበትና ግንኙነት ሊያውቅና ሊኖርበት የቻለው ክርስቶስ ብቻ ነበር፣ ምክንያቱም የአባቱን የሚመስል ተፈጥሮ (ባህርይ) ያለው እርሱ ብቻ በመሆኑ ነው፡፡ እንደ አማኞች የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን እድል ተሠጥቶናል፡፡ ነገር ግን ክርስቶስ ከጥንት ጀምሮ ዛሬም ወደፊትም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡፡

የሚከተሉ ጥቅሶች የአባትንና የልጅን ፍጹም የሆነ አንድነት የሚያሳዮት በምን መልኩ ነው? ማቴ. 11፡27፣ ዮሐ. 3፡35፣ 5፡17 እና 1ዐ፡3ዐ

_____________________________________________________________
_____________________________________________________________

የአባትና የልጅ ፍጹም ሕብረት እርስ በእርሳቸው በሙላት መተዋወቅን ያጠቃልላል፤ የፈቃድ አንድነት፣ ግብና ዓላማን ያጠቃልላል፡፡ ከዚያም በላይ የባህሪይ መመሳሰልን (አንድነትንም) ያጠቃልላል፡፡ አባትና ልጅ ሁለት አካላት ወይም ግለሰቦች ናቸው (እኔና አባቴ) ነገር ግን ተመሳሳይ ባህሪይ (“አንድ ነን”) (ከ1ኛ ቆሮ. 3፡8 ጋር ያወዳድሩ)

ክርስቶስ የመጣው እንደ ሰው ለመኖር በመሆኑ ራሱን በፈቃዱ ለአባቱ ያስገዛ መሆኑን መርሳት የለብንም፡፡ (ፊል. 2፡6-8) በእንዲህ አይነት ራሱን መገደቡ የማንነቱ መገለጫ ሳይሆን ሆን ተብሎ በዓላማ የተደረገ ነበር፡፡ በተለየ ዓላማና ግብ ክርስቶስ ራሱን ለአባቱ ሰጠ፡፡

ይህንን በአእምሮአችን ይዘን ክርስቶስ “ልጅ ከራሱ ምንም ነገር አያደርግም ከአባቱ ከሚያየው በቀር” (ዮሐ. 5፡19)፣ “የላከኝን የአባቴን ፈቃድ እንጂ የራሴን ፈቃድ አልሻም” (ዮሐ. 5፡3ዐ) ያለው ለምን እንደሆን እናስተውላለን፡፡ ይህንን ሁኔታ መሠረት በማድረግ ነበር “አባቴ ከእኔ ይበልጣል” (ዮሐ. 14፡28) ያለው፡፡

ኢየሱስ ሙሉ በሙሉ አምላክና ሙሉ በሙሉ ሰው ነበር፡፡ ይሄ አስገራሚ እውነት በሰማይና በምድር መካከል ያለውን የቅርብ ግንኙነት ምን ይነግረናል? ከዚህ የቅርብ ግኑኝነት ልናገኘው የምንችለው መጽናናት ምንድ ነው?

_____________________________________________________________
_____________________________________________________________

ማክሰኞ ሐምሌ 1, 2006 ዓ.ም

 የክርስቶስ መለኮታዊነት ክፍል አንድ

የክርስቶስ አምላክነት የእምነታችን መሠረት ነው፡፡ ሰብዓዊ የሆነ ፍጥረት ምንም ያህል ከተራው ሰው ከፍ ያለ ችሎታ ወይም ማንነት ቢኖረውም አዳኛችን ሊሆን አይችልም፡፡ በአዲስ ኪዳን በአጠቃላይ የእርሱን መለኮታዊነት ማስረጃዎችን እናገኛለን፡፡ ይህንን በተመለከተ ክርስቶስ ባስተማረው ላይ እናተኩራለን፡፡

ማንነቱን ለማወቅ ጀማሪ ለነበሩት እርሱ ማን እንደሆነ መግለጽ ቀላል ነገር አልነበረም፡፡ የእርሱ ተልዕኮ መሲህና ፣ በሥጋ የተገለጠ አምላክ መሆኑን ለዓለም ማሳወቅ የሚፈልግ ቢሆንም እርሱ በግልጽ እኔ መሲህና አምላክ (እግዚአብሔር) ነኝ ማለቱን የሚያሳይ ነገር አልተዘገበም፡፡, እንዲህ ብሎ ቢሆን ኖሮ ያኔውኑ በተገደለ ነበር፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ ለሰሚዎቹ ፍንጭና በተዘዋዋሪ መንገድ አምላክነቱን የሚረዱበትን መንገዶች ብቻ አሳያቸው፡፡

ክርስቶስ ቀስ በቀስ አምላክነቱን (መለኮታዊ ባህሪውን) ሲገልጽላቸው ብዙዎቹ ቃሎቹን የሰሙት ቢያምኑም ቀድሞ ስለ መሲሁ በአእምሮአቸው የተቀበሉትን ትምህርት በትክክል ስለማይገጥም ሊቀበሉት አልቻሉም፡፡ ይህም “እስከመቼ ድረስ እንድንጠራጠር ትተወናለህ? አንተ ክርስቶስ ከሆንህ በግልጽ ንገረን” በሚለው ጥያቄአቸው ተረጋግጧል፡፡ (ዮሐ. 1ዐ፡24) የንባቡ አውድ እንደሚያሳየን ግን ጥያቄአቸው ከልብ ለማወቅ የፈለጉ አይመስልም፡፡

ትናንት እንደተመለከትነው ከአባቱ ጋር ስላለው የተለየ ግንኙነት ክርስቶስ ብዙ ማገናዘቢያ ሃሳቦችን ሰጥቷል፡፡ ይህም አምላክነቱን ለመግለጽ ከተጠቀመባቸው ዘዴዎች አንዱ ነው፡፡ ክርስቶስ እግዚአብሔር አባቴ ነው ሲል ብዙዎች ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል መሆኑን እየነገራቸው እንደነበር በግልጽ አስተውለዋል (ዮሐ. 5፡18)፡፡

ሉቃስ 5 17-26ን ያንብቡ፡፡ ክርስቶስ አምላክነቱን ግልጽ አድርጐ ባይናገርም በምን ዓይነት ኃይለኛ መንገድ ነው ያሳየው?

_____________________________________________________________
_____________________________________________________________

“ያንን የበሰበሰ ሰውነት ወደ ቀድሞው ሁኔታ ለመመለስ ከፈጣሪነት ኃይል ያነሰ አያስፈልግም፡፡ ሰውን ከምድር አፈር ለመፍጠር የተናገረው ያው ተመሳሳይ ድምፅ ለሟቹ ሽባ ህይወትን ለመስጠት ተናግሯል፡፡ (Ellen G.white) የዘመናት ምኞት 269-270

ክርስቶስ ኃጢአትን ይቅር ለማለት ሥልጣን (መብት) እንዳለው ተናግሯል፡፡ (በማቴ. 25፡31) ደግሞ እርሱ ራሱ በዙፋኑ ላይ በክብር እንደሚቀመጥ የህዝቦችን መዳረሻ በመወሰን በሁሉም ላይ እንደሚፈርድ ተናግሯል፣ ይህንን ደግሞ ለማድረግ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ በዚህ ስፍራ በእርግጥ እርሱ ማን እንደሆነ ለማሳየት ምን ተጨማሪ ነገር አድርጓል?

እነዚያ የሃይማኖት መሪዎች ክርስቶስን በተመለከተ ምን ያህል ልባቸው ደንዳና እንደነበር አስቡ፡፡ እነዚህ ሰዎች መንፈሳዊ ነገርን በተመለከተ ህዝቡ የሚደገፍባቸው ነበሩ፡፡ እኛስ የራሳችንን መንገድ በተመለከተ ልባችን ያልደነደነ መሆኑን በምን መንገድ እርግጠኞች መሆን እንችላለን?

_____________________________________________________________
_____________________________________________________________

ረቡዕ ሐምሌ 2 2006 ዓ.ም

የክርስቶስ መለኮታዊ ባህሪይ ክፍል ሁለት

የክርስቶስ አምላክነት የእምነታችን መሠረት ነው፡፡ ሰብዓዊ የሆነ ፍጥረት ምንም ያህል ከተራው ሰው ከፍ ያለ ችሎታ ወይም ማንነት ቢኖረውም አዳኛችን ሊሆን አይችልም፡፡ በአዲስ ኪዳን በአጠቃላይ የእርሱን መለኮታዊነት ማስረጃዎችን እናገኛለን፡፡ ይህንን በተመለከተ ክርስቶስ ባስተማረው ላይ እናተኩራለን፡፡

ሌላኛው የመለኮታዊነቱ መገለጫ አስቀድሞ ስለመኖሩ በሰጠው ሃሳብ ውስጥ ይገኛል፡፡ “እርሱ ከሰማይ የወረደው” (ዮሐ. 3፡13) “አባቱ ስለላከው ነበር” (ዮሐ. 5፡23)፡፡ አስቀድሞ መኖሩን እንደገና ሲያረጋግጥ “አሁንም አባት ሆይ ዓለም ሳይፈጠር በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር አንተ በራስህ ዘንድ አክብረኝ፡፡ (ዮሐ. 17፡5)

ለምንድነው ዮሐ. 8፡58 ክርስቶስ ስለ አምላክነቱ ከተናገራቸው ዓ/ነገሮች ሁሉ ግልጽና ጥልቅ የሚሆነው? ዘፀ. 3፡13፣14ን በተጨማሪ እዩ፡፡

(“Ginomai”) የሚለው የግሪኩ ቃል ቀጥተኛ ትርጓሜ እንደሚያሳየው በእንግሊዘኛው “was” ተብሎ የተተረጐመው እየሱስ ስለራሱ ሲናገር ከአብርሃም በተቃራኒው እርሱ ቀድሞ በራሱ የነበረ መሆኑን ይገልፃል፡፡ እርሱ ከአብርሃም መወለድ በፊት የነበረ ብቻ ሳይሆን ለዘላለም የነበረ ነው፡፡ እኔ ነኝ የሚለው የሚያሳየው ቀጣይነት ያለውን ማንነቱን ነው፡፡ በተጨማሪም “እኔ ነኝ” የሚለው ስም የያህዌህ የራሱ መጠሪያ ነው፡፡ (ዘፀ. 3፡14)፡፡ መሪዎች በሚነደው ቁጥቋጦ ውስጥ እኔ ነኝ ያለው እርሱ መሆኑን በስህተት አስተዋሉት፡፡ ይህ በእነርሱ አመለካከት እግዚአብሔርን መሳደብ በመሆኑ “ሊወግሩት ድንጋይ አነሱ (ዮሐ. 8፡59)

ወንጌላት እንደሚነግሩን ክርስቶስ ያለ ምንም ተቃውሞ ከሌሎች አምልኮን ተቀብሏል፡፡ እርሱ በቅዱሳት መጻህፍት ትምህርት መሠረት ስግደት የሚገባው እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ያውቅ ነበር፡፡ ይህንንም ለሠይጣን ሂድ አንተ ሰይጣን ለጌታ አምላክህ ስገድ እርሱን ብቻም አምልክ ተብሎ ተፅፏል፡፡ በማለት ተናግሯል፡፡ (ማቴ. 4፡1ዐ) ስለዚህ ከሌሎች ስግደትን በመቀበል መለኮታዊነቱን ገልጿል፡፡ ደቀመዛሙርት በባህር (ማቴ. 14፡33)፣ የተፈወሰው ዓይነ ስውር (ዮሐ. 9፡38)፣ በክርስቶስ መቃብር አጠገብ የነበረችው ሴትዮ (ማቴ. 28፡9) እና ደቀመዛሙርት በገሊላ (ማቴ. 28፡17) ሁሉም መለኮታዊነቱን በመገንዘብ አምልከውታል፡፡ “ጌታዬና አምላኬ” የሚሉት የቶማስ ቃላት (ዮሐ. 2ዐ፡28) ቀደም ሲል አምላክነቱን በግልጽ ካልተረዳው በቀር አይሁዶች የማይናገሩትቃላት ናቸው፡፡

ዮሐ. 2ዐ፡29ን አንብቡ እስከ አሁን እርስዎ ያላዩት ነገር ግን የሚያምኑት ነገር ምንድነው? እምነትን በተመለከተ መልስዎ ምን እንድምታ አለው?

_____________________________________________________________
_____________________________________________________________

ሐሙስ ሐምሌ 3, 2006 ዓ.ም

የክርስቶስ ተልዕኮ

ክርስቶስ ማን እንደሆነ ከተረዳን በኋላ ምን ለማከናወን እንደመጣ ለመረዳት በተሻለ ሁኔታ እንሆናለን፡፡

ሰይጣን በእግዚአብሔር ላይ ክስ መሥርቷል፡፡ ክርስቶስ ለዚህ ክስ ምላሽ ለመስጠት የአባቱን ባህሪይ ለማሳየትና ስለ እግዚአብሔር በስህተት የተስተዋሉ አመለካከቶችን ለማስተካከል መጣ፡፡ የዘለዓለም ህይወት ለማግኘት እግዚአብሔርን ማወቅ በጣም አስፈላጊ በመሆኑ እግዚአብሔርን እንድናውቀው ፈለገ፡፡

ነገር ግን እንድን ዘንድ ከእውቀት የበለጠ ነገር ያስፈልገናል፡፡ እግዚአብሔር አዳኝ እንዲሠጠን ያስፈልጋል፡፡ ይህም አጭርና ግልጽ በሆነው የክርስቶስ ስም ትርጓሜ ላይ የሚገኘው ነው፤ ያህዌህ አዳኝ ነው (ማቴ. 1፡21) ክርስቶስ ተልዕኮውን ግልጽ በሆኑ አባባሎች ገልጿል፡፡ “የሰው ልጅ የመጣው የጠፋውን ለመፈለግና ለማዳን ነው” (ሉቃስ 19፡1ዐ) በኤደን ገነት የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸውን ግንኙነት፣ ቅድስናቸውን፣ ቤታቸውን እና የዘላለም ህይወታቸውን ጭምር አጥተዋል፡፡ ኢየሱስ ሁሉንም ነገር እንደገና ለማደስ መጣ፡፡ ከአባቱ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማደስ (ዮሐ. 1፡51) ኃጢአታችንን ይቅር ለማለት (ማቴ. 26፡28) እንዴት መኖር እንዳለብን ምሳሌ ለመስጠት (1ኛ ጴጥ. 2፡21)፣ በእርግጥ ደግሞ የዘላለምን ህይወት ዳግም ይሠጠናል ዮሐ. 3፡16

ኢየሱስ የተልዕኮውን ፍሬ ነገር የገለፀው እንዴት ነበር? ዮሐ. 1ዐ፡11፤ ማቴ. 2ዐ፡28 ያንብቡ፡፡ እየሱስ መሞት ለምን አስፈለገው? ምክንያቱ እርሱ የእኛን ሥፍራ ስለወሰደ እና ለእኛ የሚገባዉን የኃጢአት ቅጣት በፈቃዱ ስለተሸከመ ነዉ፡፡ እኛ ሁላችንም ኃጢኣተኞች ነን (ሮሜ 3፡1ዐ-12) በዚህ ምክንያት ሞት ይገባናል (ሮሜ 6፡23)፡፡ የመዳናችን ዋጋ እጅግ ታላቅ ከመሆኑ የተነሳ ሊከፈል የሚችለውና (በቂ) የሚሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ህይወት ብቻ ነው፡፡

የተጣሰው የእግዚአብሔር ህግ የኃጢአተኛውን ህይወት ይፈልጋል፡፡ በዓለማት (ዩኒቨርስ) ሁሉ በሰው ፈንታ ሆኖ ይህንን ጥያቄ የሚመልስ አንድ ብቻ ነበር፡፡ የመለኮታዊ ህግ ልክ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ በመሆኑ ይህንን የመተላለፍ ዋጋ ሊከፍል የሚችለው ከእግዚአብሔር ጋር እኩል የሆነው ብቻ ነው፡፡ የወደቀውን ሰው ለመዋጀትና ከኃጢአት እርግማን አውጥቶ እንደገና ከሰማይ ጋር ተስማሚ እንዲሆን የሚያስችለው ሌላ ማንም ሳይሆን ክርስቶስ ብቻ ነው፡፡” (አበውና ነቢያት ገጽ 63)

ዙሪያዎትን ዓለማችንንና የእኛንም በዓለም ላይ ያለንን ዕድል ፋንታ ይመልከቱ፡፡ ሁሉም ነገር በመቃብር ወይም በሞት የሚያበቃ ቢሆን ተስፋችን ምን ይሆን ነበር? የመዳን ዕቅድ ባይዘጋጅልን ኖሮ ምንም ተስፋ አልነበረንም ታዲያ እግዚአብሔር በክርስቶስ አማካይነት ላደረገልን ነገር ደስታችንን የምንገልጽለት እንዴት ነው?

_____________________________________________________________
_____________________________________________________________

ዓርብ ሐምሌ 4, 2006 ዓ.ም

ለተጨማሪ ጥናት፡- ኤለን ጂ. ኋይት “መለኮታዊ ሰብዓዊ አዳኝ” ገጽ 1126- 1128 የአድቬንቲስት የመጽሐፍ ቅዱስ መግለጫ ጥራዝ 5

“መጽሐፍ ቅዱስ በምድር ላይ ስለነበረ የክርስቶስ ሰብዓዊነት ሲናገር ቀድሞ የነበረ ስለመሆኑም አስረግጦ ይነግረናል፡፡ ቃልም መለኮታዊ አካል ሆኖ ከጥንት ነበር እንደ እግዚአብሔር ልጅ እንዲያውም ከእግዚአብሔር አባቱ ጋር በፍጹም ህብረት ዓለም በእርሱ ተፈጠረ ከሆነዉም አንዳች ያለእርሱ አልተፈጠረም (ዮሐ. 1፡3)፡፡ ክርስቶስ ሁሉንም ነገር ከፈጠረ እርሱ ከሁሉም በፊት ነበር፡፡ ስለዚህ የተነገሩ ቃላት ማንም በጥርጣሬ ውስጥ እንዳይተው በጣም ወሳኝ ናቸው፡፡ ክርስቶስ በትክክል እግዚአብሔር ነው፡፡ እርሱ ዘላለምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ነበር በሁሉም ነገር ላይ እግዚአብሔር ነው ለዘላለም የተባረከ ነው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊው የእግዚአብሔር ልጅ ከጥንት የነበረ፣ የተለየ ማንነት ያለው ሆኖም ግን ከአባቱ ጋር አንድ የሆነ ነው:: (Ellen.G.white Selected messages) book 1.p 247)

የክርስቶስ ህይወት ከማንም ያልተዋሳት የራሱ የሆነች ህይወት ናት፤ 1ኛ ዮሐ. 5፡12 የክርስቶስ መለኮታዊነት ለአማኞች የዘላለም ህይወት ዋስትና ነው፡፡ የዘመናት ምኞት ገጽ 53ዐ

የመወያያ ጥያቄዎች፡-

  1. እርኩሳን መናፍስት ኢየሱስ “የእግዚአብሔር ቅዱስ“ (ማር. 1፡24) የእግዚአብሔር ልጅ ማር. 3፡11 “የልዑል የእግዚአብሔር ልጅ” (ማር. 5፡7) መሆኑን ይመሰክራሉ፤ ያዕ. 2፡19 በተጨማሪ ይመልከቱ፡፡ ልክ በተመሳሳይ ሁኔታ ኢየሱስ ጌታ መሆኑን መመስከር ብቻውን ለመዳናችን በቂ የማይሆነው ለምንድነው? ኢየሱስ ጌታ መሆኑን ማወቃችን ብቻ በቂ ነው የሚለውን አመለካከታችንን ልናስወግደው የምንችለው እንዴት ነው?
  2. በክርስቶስ አንፃር ቆሞ የነበረው የመቶ አለቃ እንዴት ሆኖ ነፍሱን እንደሰጠ ባየ ጊዜ “እውነትም ይህ ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ነው” አለ (ማር. 15፡39) የሱስን ከሁሉ በተሻለ ሁኔታ ለመረዳት ትክክለኛው ሥፍራ መስቀሉ ግርጌ ነው፡፡ ወደ መስቀሉ ግርጌ በስንት ጊዜ ይሄዳሉ? እዚያ ስፍራ ለመጨረሻ ጊዜ ሄደው የነበረው መቼ ነው? ታዲያ አሁን በዚሁ ቅጽበት ለእርስዎ ስለከፈለው መስዋዕትነት ለማሰላሰል ለምን ጊዜ አይወስዱም?
  3. በክርስቶስ ዘመን የነበሩ ብዙዎች ስለ መሲህ የነበራቸው ግንዛቤ ትክክለኛ ስላልነበር ክርስቶስን አልተቀበሉትም፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ ዛሬም ብዙዎች ቀደም ሲል ስለ ክርስቶስ ያላቸው አስተሳሰብ ትክክለኛ ባለመሆኑ ህይወታቸውን ለእርሱ ለማስረከብ እምቢ ብለዋል፡፡ እነርሱ ክርስቶስን በትክክል እርሱነቱን ማየት ይችሉ ዘንድ እንዴት ልንረዳቸው እንችላለን?

 

 

Copyright © 2013 Ethio SDA . All Rights Reserved