ከሰኔ 7-13 2006 ዓ.ም
ሰንበት ከሰዓት
የሚከተሉን ጥቅሶች ለዚህ ሰንበት አንብቡ፡- ዘፍ. 2፡16፤ 3፡7፤ ዘፍ. 6፤ ዘፍ. 12፤ ዘዳ. 7፡6-12፤ ገላ. 3፡6-15፤ ራዕይ 12፡ 7፤ ራዕይ 14፡6-12
የመታሰቢያ ጥቅስ፡- ‹‹የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የሚጠብቁት ኢየሱስንም በማመን የሚፀኑት ቅዱሳን ትዕግሥታቸው በዚህ ነው›› (ራዕይ 14፡12)፡፡
በራሊ ውድድር ላይ ቡድኑ አራት ራጮች ይኖሩታል፡፡ በሌላ ጊዜ የቡድኑ አባላት እርስበርሳቸው ይፎካከራሉ ነገር ግን አሁን አንድ ቡድን ስለሆኑ እንደአንድ ሆነ ማሰብ ይጀምራሉ፡፡ የውድድሩ ርቀት ለአባላቱ በእኩል መጠን የተከፋፈለ ነው፡፡ የሚቀባበሉት ዱላ ውድድሩ እስኪያልቅ ድረስ ከአንዱ የቡድን አባል ወደሌላኛው ይተላለፋል፡፡ ይህም ማለት በውድድሩ ላይ ለሚካፈሉ አባላት በሙሉ የውድድሩን ቀጣይነት የሚያረጋግጠው ምልክት ቢኖር የሚቀባበሉት ዱላ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያንም ልክ አንደ ዱላ ቅብብሉ ውድድር ቡድን ነው፡፡ ከኤደን የአትክለት ስፍራ አዳም አንስቶ ይህ ዱላ በተለያዩ የድነት ታሪኮች ውስጥ በብዙ ደረጃ እያለፈ መጥቷል፡፡ ከኖህ እስከ አብረሃም ከሲና እስከ አዲስ ኪዳናዋ ቤተክርስቲያን ከተሃድሶ ንቅናቄ ቤተክርስትያን እስከ አሁንዋ የሶስቱን መላእክት መልዕክትን እሰከሚያውጁት ድረስ ቀጥሏል፡፡
የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ቀጣይነትን የሚያረጋግጥልን ምልክት ደግሞ ህጉ ነው፡፡ ከውድቀት በኋላ ሁላችንም እግዚአብሔር የማዳን ፀጋው ውስጥ ልንሆን ይገባናል፡፡ ሁለቱም ማለትም ህግ እና ፀጋ የወንጌል አስፈላጊ ነጥቦች ናቸው፡፡
በዚህ ሳምንት ትምህርታችን በዘመናት ሁሉ የእግዚብሄር ህግ (ፀጋ) ቀጣይነት ኖሮት እየዘለቀ እንደሄደ እናያለን፡፡ የዚህን ሳምንት አጥንተው ለሰኔ 14 ሰንበት ይዘጋጁ፡፡
ዕሁድ ሰኔ 8 2006 ዓ.ም
ከአዳም አንስቶ እሰከ ኖህ
‹‹የክርስቶስ ቤተክርስቲያን›› ብለን መናገር የምንችለው ከአዲስ ኪዳን ዘመን አንስቶ ነው፡፡ ይሕም አማኞች ስለየሱስ ህይወት፤ ሞት እና ትንሳኤ ለመጀመርያ ጊዜ የመሰከሩበት ወቅት ነው፡፡ ያም ቢሆን ግን ‹‹የክርስቶስ ቤተክርስቲያን›› ሰፋ ባለ አውድ እናየዋለን የግሪኩ ቃል ቤተክርስቲያንን አክሌሺያ (ekklesia) ይለዋል፡፡ ይህም ቃል የተወሰደው ከዓለማዊ ቋንቋ ሲሆን የሚያመላክተን ነገር ቢኖር ‹‹የተጠሩ›› ማለት ነው፡፡ በየትውልዱ እግዚአብሔር በታማኝነታቸው፣ እምነታቸው ፍቅራቸውና ታዛኝነታቸው የእርሱን ፈቃድ የሚያንፀባርቁ ሰዎችን ጠርቷል፡፡
ዘፍ. 2፡16፤ 3፡7ን አንብቡ፡፡ ለአዳምና ሔዋን የተሰጣቸው ፈተና ምን ነበር? ፍፁማዊ ሰው መሆናችንን ለማረጋገጥ እነዚህ አይነት ፈተናዎች ለምን አስፈለጉ?
————————————————————————————
————————————————————————————
አዳምና ሔዋን ማፍቀር እንዲችሉ ሆነው የተፈጠሩ ነፃ ፍጥረቶች ነበሩ፡፡ አሳማኝ ምክንያት ባይኖራቸው እንኳን ስህተትን ለመፈጸም በቂ ችሎታና ነፃነት ተሰጧቸዋል፡፡ የዘፉ ፍሬ ፈተና የሞራል ፈተና ነበር፡፡ እግዚአብሔር የሰጣቸውን የሞራል (ግብገባዊ) ነፃነት እንዴት ነበር የተጠቀሙት? ምላሹን እናውቀዋለን፡፡
የግብረ-ገባዊነት ማዕከሉ ህግ ነው ይህም የእግዚአብሔር ህግ መልካሙንና ክፉውን በዝርዝር ይገልፅልናል (አስታውሱ ዘፍዋ መልካሙንና ክፉውን የምታሳወቅ ነበረች) የህጉ አላማ መዋሸትን፤ መስረቅን እና መግደልን መከልከል ነው፡፡ ሰብአዊ የሆኑ ፍጡራን እነዚህን መጥፎ ነገሮች ለመስራት ችሎታ ባይኖራቸውና መልካምን ነገር ብቻ ማድረግ ቢቻላቸው ህጉ በዚህ ዓለም ላይ ያለው ትርጉም ዋጋ ቢስ በሆነ ነበር፡፡
ነገር ግን እግዚአብሔር በእውነተኛ ፍቅር ስለወደደን ሁሉን ለማድረግ እንድንመርጥ አድርጐ ፈጠረን፡፡ አዳምና ሔዋን ከወደቁ በኋላ እንኳን ለሚቀጥለው ትውልድ ‹‹ይህንን ዱላ›› አስተላለፉ በዚህ ጊዜ የሰብአዊነት ግብረገብ በፍጥነት የዘቀጠበትና የቆሸሸበት ጊዜ ነበር፡፡ ከመጀመርያ ሁለት ልጆቻቸው መካከል አቤል ብቻ ነበር የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን ለመከተል የወሰነው፤ ቃየን ግን በምኞት፤ ሀሰት፤ ገድያ እና ወላጆችን ባለማክበር መንፈስ ውስጡ ተሞላ፡፡ ነገሮች የበለጠ እየከፋ ሄደው ክፉ መንፈስ በመልካሙ ነገር ላይ ጥላ ለማጥላት ሸፈነው በውሃ ጥፋት ጊዜ ኖህና ቤተሰቡ ብቻ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን አባል በመሆን ምርጫቸውን አፀኑ፡፡
ከኤደን ገነት አንስቶ በተሰጠን ነፃነት አማካኝነት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ምን ያህል ጊዜ ነው የሞራል ምርጫዎችን ማድረግ የቻሉት? እነዚህ ምርጫዎች ምን ነበሩ? ከእግዚአብሔር የሞራል ህግ ጋርስ ምን ያህል ይጣጣማሉ?
ሰኞ ሰኔ 9 2006 ዓ.ም
ከኖህ አንስቶ እስከ አብርሃም ድረስ (ዘፍ. 6፡5-9)
ኖህ ሲወለድ የነበረው አለም እጅግ በጣም የከፋ አለም ነበር፤ በዛን ወቅት የነበሩ ማህበረሰቦ በክፋት ተሞልው ነበር፡፡ ከሺህ አመታት በፊት ይኖሩ የነበሩ ህዝቦች ላይ እግዚአብሔር ማዘኑን ስናይ እርኩስ መንፈስ ምን ያህል ማህበረሰቡን ስር በሰደደ ክፋት እንደሞላቸው እንመለከታለን፡፡
ዘፍ. 6ን አንብቡና የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ፡፡
እግዚአብሄር ሰውን በመፍጠሩ ‹›አዘነ›› የሚለውን ሀሳብ እንዴት ነው የምንረዳው? እግዚአብሔር አምላክ ይህ ነገር እንደሚሆን ምንም ነገር አያውቅም እያል እንዳልሆን እንዴት እንገልጻለን? (ዘዳ. 31፡15-17)
————————————————————————————
————————————————————————————
ኤለን ጂ. ኋይት ሰትጽፍ ‹‹የእግዚአብሔር ልጆች›› እና ‹‹የሰው ልጆች›› የሚለውን አባባል ታማኝ የሆኑ ሰዎች ታማኝ ያልሆኑ ሴቶችን አገቡ ብላ ታብራራለች፡፡ ቤተክርስቲያን ከአለም ጋር ስላላት ግንኙነት በተመለከተ ምን መምሰል እንዳለባት ከዘፍ. 6 ምን እንማራለን?
————————————————————————————
————————————————————————————
እግዚአብሔር የማያስደስቱ ምን ምን ነገሮችን ነው እነዚህ ሰዎች ያደረጉት? ይህስ ከህጉ ጋር እንዴት ይዛመዳል?
————————————————————————————
————————————————————————————
በዘፍ. 6 ላይ ስለ ኖህ የተዘገበውን ነገር ተመልከቱ፡፡ በተለይ በዛ በተበከለ አለም ውስጥ ስለ ኖህ ማንነት ይህ ጥቅስ እንዴት እንድናስተውል ይረዳናል? በተመሳሳይ ጊዜ ኖህ በእግዚብሔር አይን ፊት ‹‹ፀጋ›› ያስፈለገው ለምን ነበር? በዛን ጊዜ እንኳን በእምነት እና በእግዚአብሔር ህግ መካከል ስለነበረው ግንኙነት ምን የሚነግረን ነገር አለው?
————————————————————————————
————————————————————————————
ማክሰኞ ሰኔ 10 2006 ዓ.ም
ከአብርሃም አንስቶ እስከ ሙሴ
ከጥፋት ውሃ በኋላ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በትውልዱ ሁሉ ለማካፈል ሃላፊነት የተጣለባቸው በኖህ ልጆቹ ላይ ነበር፤ የኖህ ቤተሰቦች ይህንን አይነት አለማቀፋዊ ጥፋት ያስተናገዱት ሰብአዊ ዘር የእግዚአብሔርን ህግ በመቃወሙ በመሆኑ የእግዚአብሔርን ፀጋ በመለማመድ ታማኝ የሆኑ ትውልዶችን ለመፍጠር አንድ ነገር ማድረግ ይችሉ ነበር፡፡ የሚያሳዝነው ግን የጥፋት ውሃ አልፎ ብዙም ሳይቆይ የምድር ነዋሪዎች አመፁ (ዘፍ. 11፡1-9) ‹‹ብዙዎች የእግዚአብሔርን መኖር ካዱ የውሃ ጥፋቱም ተፈጥሮአዊ ክስተት እንደሆነ ቆጠሩ፡፡ ሌሎች ግን ሃያል በሆነው አምላክ በሃጢያት የተሞላውን አለም ያጠፋው እርሱ እግዚአብሔር እንደሆነ በማወቅ ልባቸው ልከ እንደ ቃየን በእግዚአብሔር ላይ በአመፅ ተነሳሳ›› Ellen G. white, patriarchs and prophets, P. 119
ዘፍ. 12 እና 15፡1-6 ህግ እና ፀጋ እንዴት አብረው እንደሚሄዱ ምን ይነግሩናል?
————————————————————————————
————————————————————————————
የተራ ትውልድ የሆነው አብርሃም ከእግዚአብሔር ጋር የባርኮት ቃል ኪዳን ተሰጠው (ዘፍ. 12፡1-3) መጽሐፍ ቅዱሳችን ስለአብርሃም መጠራት መስፈርት ምንም የነገረን ነገር የለም፡፡ እንደኖህ የጽድቅን ኑሮ በመመላለሱ አልነበረም የተጠራው ፡፡ እንደውም ከጥሪው በኋላ አታላይ ሆኖ ተገኝቶ ነበር (ዘፍ. 12፡11-13) የእግዚአብሔርን ህግ በመጣስ የሆነው ነገር ቢሆን እንኳን አብርሃም እውነተኛ እምነት የነበረው ሰው ነበር፡፡ የእግዚአብሔርም ፀጋም ይህንን እምነቱን እንደፅድቅ ቆጠረለት፡፡ ምንም እንኳን ፍጹም ባይሆን በሰዎች እይታ የማይቻሉትን ነገሮች ለእግዚአብሔር እንደሚቻሉት በማመን የእርሱን ድምጽ
ለመስማት ፈቃደኛ ሆነ፡፡
የእግዚአብሔርን ድምፅ ከሚሰሙ እና ትዕዛዛቱን ከሚታዘዙት መካከል አብርሃም ብቸኛው ግለሰብ አልነበረም፡፡ ፈርኦን፤ ሁለቱ አቢሜሊኮች እና ዮሴፍ እግዚአብሔር አመንዝራነትንና ሀሰትን እንደማይደግ ተገንዘበዋል፡፡ ሁለተኛው አቢሜሌክ አንደውም የአቤሜሌክ የሆኑትን ህዝቦች ይስሃቅ ለፈተና እንዲጋለጡ በማድረጉ ገስፆታል፡፡ ምንም እንኳን እግዚአብሔር አብርሃምን ለተለየ ተግባር ቢመርጠውም በተለያየ ቦታ ግን እግዚአብሔርን የሚፈሩ ህዝቦች በእርግጥም አብርሃም ከሎዶጐምርንና ከእርሱ ጋር አብረው የነበሩትን ነገስታት በጦር ሃይሎች አማካኝነት ካሸነፈ በኃላ የልኡል እግዚአብሔር ካህን በሆነው መልከፄዴቅ አማካኝነት ተባረከ (ዘፍ. 14፡18)፡፡ ይህም ከሙሴ ተግባር እና የወንጌል እንቅስቃሴ በፊት እንኳን በዛን ጊዜ እንኳን በነበረው አለም እግዚአብሔርን የማወቅ እውቀት እንደነበራቸው ማረጋገጫን ይሰጠናል፡፡
ረቡዕ ሰኔ 11 2006 ዓ.ም
ከሙሴ አንስቶ እስከ የሱስ
በግብፅ እና ሜስፓታሚያ ጥንታዊ ህግጋቶች መገኘታቸው ስለእግዚአብሔር ህግ ሰፋ ያለ እይታ እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ የሆነው ሆኖ ግን አንዳቸውም ህጐች ፍፁም ቢሆኑ የሆኑ ህጐች አይደሉም፡፡ በትክክልም ከእነዚህ ህግጋቶች መካከል የጣኦት አምልኮን የሚያበረታቱ ህግጋቶች ያሉ ሲሆን እግዚአብሔር ደግሞ በኃላ ላይ ይህንን ነገር ፈፅሞ ይኮንናል፡፡ ስለዚህ እግዚብሔር ህዝቦቹ የህጉ እውነተኛ መጋቢ (ባለአደራ) ይሆኑ ዘንድ መርጧቸዋል፡፡ እነዚህም ህዝቦች እብራዊያን ሲሆኑ የአብርሃም ዘር ትውልዶች ከብዙ አመታት ቀደም ብሎ የተነገረውን ቃልኪዳን የወሰዱ ህዝቦች ናቸው፡፡ የዚህም ቃል ኪዳን ዋነኛ ፍፃሜ የሚገኘው በየሱስ ውስጥ ነው፡፡
ዘዳ. 7፡6-12 አንብቡ፡፡ ይህ ጥቅስ በህግ እና ፀጋ መካከል ያለውን ግንኙነት እንዴት ይገልጻል ?
————————————————————————————
————————————————————————————
እግዚአብሔር እስራኤላዊያን ህጉን ጠብቀው እንዲቆዩ ሲያደርግ ፍጹም ያልሆኑ ህዝቦች እንደነበሩ ያውቃል፡፡ ቢሆንም ግን ከሌሎች ፍፁማን ካልሆኑ ህዝቦች ጋር የእግዚአብሔርን ፍቃድ የማካፋል ተግባርን አምኖ ሰጣቸው፡፡ ‹‹የካህናት መንግስትና የተቀደሰ ህዝብ›› ተብለው የተጠቀሱት እራኤላዊያን (ዘፀ. 16፡6) መላውን አለም ከእግዚአብሔር ጋር አስታራቂ የሆኑ ካህናት እንዲሆኑ ነው፡፡ እስራኤል የተጠራው የእግዚአብሔርን እውነተኛ ፈቃድ ግራ ለገባው አለም እንዲያስታውቁ ነው፡፡ ነገር ግን እስራኤል በስህተት፣ በውድቀትና፣ በአመፅ የተሞሉ ህዝቦች ቢሆንም መሲሁ ግን ከነርሱ መካከል ተወልዶ፤ ወንጌልን ሰብኮ እና ሞቶ ከአያሌ አመታት በፊት ለአብሃርሃም የተገባለትን የቃል ኪዳን ተስፋ ፈፀመ፡፡
ገላ. 3፡6-16 ያለውን አንብቡ፡፡ ጳውሎስ የጻፈው ፅሁፍ እንዴት አድርጐ ነው የቃል ኪዳን ተስፋን ትርጉም በተሻለ መልኩ እንድንረዳ የሚያደርገን ?
————————————————————————————
————————————————————————————
በጥንት እስራኤላዊያን መረዳት ‹‹ዘር ›› የሚለው ነጠላ ቃል እስራኤልን አንደ ብቸኛ ህዝብ የሚገልፅ ትርጉሙም አለው፡፡ ጳውሎስ እዚህ ጋር የሱስን እንደእወነተኛ የቃል ኪዳኑ ተስፋ መፈፀሚያ አድርጐ ይገልፀዋል፡፡ ስለዚህ ወንጌል በራሱ በግልፅ ሲተነተን ህግ እና ፀጋ በሙላት ቃል ኪዳኑን ይገልፃሉ፡፡
ከረጅም ዘመናት በፊት አብርሃም ቃል ኪዳኑን ከተቀበለበት ጊዜ አንስቶ እስከ ክርስቶስ ጊዜ ድረስ ያሉትን አመታት እስቲ አስቡ፡፡ እግዚአብሔርን ስናምን ምን ያህል ታጋሽ መሆን እንዳለብን እንዴት ያስረዳል ?
ሐሙስ ሰኔ 12 2006 ዓ.ም
ከየሱስ አንስቶ እስከ ቅሬታዎቹ ህዝቦች
ከኤደን ገነት ጀምሮ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን በወደቁ ሰዎች የተሞላች ነበረች፡፡ የእግዚአብሔርን ጽድቅ ለመመስከር የተነሱ ተቋማት እንኳን ያው ጽድቅ ለራሳቸው ያስፈልጋቸው ነበር፡፡ ይህ ‹‹ዱላ›› ከትውልድ ወደ ትውልድ በሚተላለፍበት ሰዓት ማንም ተወዳዳሪ (ሯጭ) የመጨረሻውን የማሸነፊያ መስመር አልፎ መግባት አልተገባውም፡፡ ህጉን የተቀበሉ ሰዎች በሙሉ እንኳን ወደ ጽድቅ ደረጃ መድረስ አልተቻላቸውም፡፡ ሰብአዊነት በከንቱነት ወጥመድ ስር ወድቆ ታየ፡፡
ሁሉም ተስፋ ተማጦ የጠፋ ቢመስልም እግዚአብሔር ‹ዱለውን›› ለመረከብ ልጁን ላከ፡፡ ሁለተኛው አዳም የሆነው የሱስ ያለ ኃጢያት በዚህ ምድር ተመላለሰ፡፡ ከአባቱ ጋር ካለው ፍፁማዊ የመሰጠት ግንኙነት የተነሳ እስከ መስቀል ድረስ ታዛዥነቱን ይዞ ቀጠለ፡፡ በትንሳኤው አማካኝነት የሱስ የመጨረሻውን የማሻነፍያ መስመር አልፎ ገባ፡፡ በዚህም የሞትን ሰንሰለት በጠሰ፡፡ አሁን በመንፈስ ሃይል ከሞት የተነሳው የሱስ ፅድቁን ለአማኞች በሙሉ አካፈለ፡፡ ይህ መልእክት ሁልጊዜ የቃል ኪዳኑ የተስፋ ቃል ማዕከል መሆኑ የተስተዋለው የሱስ ስራውን ከፈፀመ እና የአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ከጀመረ ወዲህ ነው፡፡
የሚያሳዝነው የክርስትያኖች ቤተክርስቲያን በዚህ ብርሃን የተሞላች ቢሆንም ከጥንታዊያን እስራኤሎች በበለጠ ለቃል ኪዳኑ የነበራቸው ታማኝነት እጅግ ዝቅተኛ ሆነ፡፡ ስለዚህም ሃይማኖትን እየተው መሄድ በየቦታው ተንሰራፋ፡፡ በአስራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን የተሃድሶ እንቅስቃሴ መጀመር ይህንን አካሄድ ለወጠው፡፡ ይህም ቢሆን ግን የሀሰት አስተምህሮዎች እና ትምህርቶች በክርስቲያኑ ዓለም ውስጥ እየቀጠሉ ሄዱ፤ ይህ የሀሰት ትምህርት ከሚያካትታቸው ሀሳቦች መካከል አንዱ የህጉን ሚና እና አላማ በአዲስ ቃልኪዳን ውስጥ የነበሩ አማኞች በስህተት መገንዘባቸው ነው፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር ብዙ የጠፉ እውነተኞችን የሚመልሱ ቅሬታ የሆኑ ህዝቦችን ጠራ፡፡
ዘፍ. 12፡17 እና 14፡6-12ን አንብቡ፡፡ እነዚህ ጥቅሶች ህግንና ፀጋን ከእግዚአብሔር የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ጋር በማድረግ እንዴት ገለፀልን?
————————————————————————————
————————————————————————————
ከላይ እንዳየነው ‹‹የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ‹‹መጠበቅ እውነተኛውን ፍቅር የምንገልፅበት መንገድ ነው፡፡ በዚህ መንገድ በውጪያዊነት ትዕዛዛቱን ብንጠብቅም ፍቅርን ግን እንደሚገባን መግለጥ አልቻልንም? ፍቅርን የማናሳይ ከሆነ ለምንድነው ታዲያ ትእዛዛቱን የምንጠብቀው?
ዓርብ ሰኔ 13 2006 ዓ.ም
ተጨማሪ ጥናት፡- ‹በራዕይ ላይ የሚገኘው የሶስቱ መላእክት መልእክት የሚወክለው የእግዚአብሔርን የመልዕክት ብርሃን ተቀብለው እርሱን በመወከል እስከ ምድሪቱ ስፋት ጥልቀት ድረስ ይህንን ማስጠንቀቂያ ይዘው የሚሄዱ ህዝቦችን ይገልፃል፡፡
ክርስቶስ ለተከታዮቹ እንዲህ ይላቸዋል ‹‹እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ›› (ማቴ. 5፡14) የሱስን ለተቀበለ ነፍስ ሁሉ የቀራንዮ መስቀል ሲጣራ ለነፍሳቶች ሁሉ ‹‹ወደ አለም ሂዱ ወንጌልንም ስበኩ ለፍጠረታት ሁሉ›› (ማር. 16፡15) ይለናል፡፡ ይህንን ስራ ሊያደናቅፍ የሚችል ምንም ነገር አይኖርም፡፡ በዚህ ጊዜ ይህ ስራ እጅግ በጣም አስፈላጊ ስራ ነው፡፡ ለነፍሳት ሁሉ በሆነው መስዋዕትነት ፍቅርን የሱስ ሲገልጽ መዋጀታቸውን ፈጽሞ የርሱን ተከታዮች አነሳሳ›› Ellen G. white, Testimonies for the church ,vol. 5, pp 455-456.
‹‹የሶስተኛው መላዕክት መልዕክት አስፈላጊ ፍሬ ሀሳብ የአንደኛውን እና የሁለተኛውን መልኣክ መልዕክት ያቀፈ ነው፡፡ በነዚህ መልዕክቶች ውስጥ ያለውን እውነት ሁሉም ሰው አስተውሎ በየቀን ህይወቱ ተግባራዊ ሊያደርገው ይገባል፡፡ ምክንያቱም ይህ ለድነታችን በጣም አስፈላጊ ነውና፡፡ በሙሉ ፍላጐት እና በጸሎት በማጥናት እነዚህን እውነቶች ልንረዳቸው ያስፈልገናል፡፡ እንድንማር የሚያደርገን ከላይ ከሰማይ የመጣ ሃይል ነው፡፡›› Ellen G. white, evangelism, p. 196
የመወያያ ጥያቄዎች፡-
- ራዕይ 12፡17 ‹‹ቅሬታዎችን›› ሲገልጻቸው የእግዚአብሄርን ትዕዛዛት የሚጠብቁእና የየሱስ ሃይማኖት ያላቸው ብሎ ነው፡፡ በዓለም ላይ ከሚገኙት በመቶዎች ከሚቆጠሩ ሰንበትን ከሚጠብቁ ቤተክርስትያኖች መካከል የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት የተለየ አለማዋ ምንድነው? ሌሎች ቤተክርሰቲያናት ሰንበትን እየጠበቁ ቢሆንም ትክክል እንዳልሆኑ የምንናገረውና የምናስተምረው ምንን ነው?
- ሮሜ 4፡3፤ ገላ. 3፡6 እና ያዕ. 2፡23ን በአውዳቸው መሰረት አንብቡ፡፡ እነዚህ ጥቅሶች ድነት በእምነት መሆኑን እንደናስተውል እንዴት ያግዙናል?
- በመጀመርያው መልአክ መልዕክት ላይ እንደምናሰተውለው ‹‹የዘላለም ወንጌል›› በማለት ይጀምራል፡፡ ‹‹የፍርዱ ሰዓት ደርሶአል›› ብሎም ያውጃል፡፡ ስለዚህ ወንጌል፣ ህግ እና ፍርድ በሶስቱ መላዕክት መልእክት ውስጥ በአንድነት ተገልፀዋል፡፡ እንዴት ነው ታዲያ በፍርድ ሰዓት የህግንና ፀጋን ሚና ማስተዋል የምንችለው? ሁሉም በአንድ ላይ ሆነው እንዴት ሊሄዱ ይችላሉ?