11ኛ ትምህርት: ሐዋሪያትና ህጉ

SSL 11

ሰንበት ከሰዓት
ለዚህ ሳምንት ትምህርት፡- ሮሜ 3፡31፤6፡15 የሐዋ. ሥራ 10፡9-14፤ ዮሐንስ 15፡1-11፤
ያዕቆብ 2፡1-26፤ ዕብ. 3፡7-19፤ ይሁዳ 5-7ን ያንብቡ፡፡

መታሰቢያ ጥቅስ፡- ‹‹ስለዚሀ ህጉ ቅዱስ ነው ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጐም ናት›› (ሮሜ 7፡12 )

እግዚብሔር ህግ አስፈላጊነት ቀጣይ ለመሆኑ ብዙ ማስረጃዎች ቢኖሩም ብዙ ክርሰቲያኖች በተቃራኒው የሚከራከሩት ለምንድነው? በመጀመርያ አንዳንዶች ከአዲስ ኪዳን የህጉን ተግባር በስህተት መረዳትን የሚያወግዙ ጥቅሶችን እየተመለከቱ ችግሩ ከህጉ ነው ብለው ይደመድማሉ፡፡ በውጤቱም በአዲስ ኪዳን ስር ላሉ  ሁሉ አስርቱ ትዕዛዛት ግዴታ አይደሉም ብለው ያስተምራሉ፡፡
በሁለተኛ ደረጃ ሌሎች ሰንበት ለክርስቲያኖች የግድ እንዳልሆነ ከማመናቸው የተነሳ ይህንን አሳባቸውን ለማስረገጥ ሁሉም ትዕዛዛት ከየሱስ ጋር በመስቀል ተሰቅለዋል ይላሉ፡፡

ሶስተኛው አንደንዶች ሌሎቹ ዘጠኙ ያስፈልጋሉ አራተኛው ግን ማለትም ሰባተኛው ቀን ሰንበት ግን የኢየሱስን ትንሳኤ ለማስታወስ ሲባል በእሁድ ተቀይሯል ብለው ይሞግታሉ፡፡ ከላይ በጠቀሱት አቋሞች ላይ ብዙ ጥያቄ የሚያስነሱ ነገሮች አሉ፡፡ በዚህ ሳምንት የክርስቶስ ሐዋርያት ስለ ህጉ ያላቸውን አመለካከት እንመለከታለን፡፡ ምክንያቱም ከክርስቶስ ሞት በኋላ የሚሻር ቢሆን ኖሮ ሐዋርያቱ ስለዚህ ነገር ማወቅ ነበራቸው፡፡

የዚህን ሳምንት ትምህርት አጥንተው ለሰኔ 7 ሰንበት ይዘጋጁ፡፡

እሁድ               ሰኔ 1 2006 ዓ.ም

ጳውሎስና ህጉ

ጳውሎስ እውነተኛው የክርስትና መስራች ነው ተብሎ ይናገራል፡፡ ይህ በእርግጥ ስህተት ነው፡፤ ጳውሎስ ከ 27ቱ የአዲስ ኪዳን መጽሐፍት 13ቱን በመጻፍ የክርስትናን አስተምህሮ እንድናስተውል የበኩሉን ብዙ አሰተዋጽኦ ቢያደርግም በርሱ ጽሁፎች ውሰጥ ያሉት ትምህርቶች በሌሎች  የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍሎች የሚገኙ ናቸው፡፡ ጳውሎስ ‹‹አዲስ› እምነት ጀምሯል ብለው አንዳንዶች እንዲያስተምሩ ምክንያት የሆነው ስለ ህግና ሰለፀጋ እሱ ያስተማረውን በስህተት በመረዳታቸው ነው፡፡ ሮሜ 3፡28፤ 6፡14፤ 7፡4 እና ገላ. 3፡24፤25ን ይመልከቱ በመጀመርያ ሲታይ እነዚህ ህጐች መሻሩን ያስረዳሉ ብሎ ማመን ለምን ይቀላል? ለይተው ያንብቧቸው፤ እነዚህ ጥቅሶች በእርግጥም ህጉ ለክርስቲያን አያስፈልግም የሚልን መልእክት ይሰጣሉ፡፡ ሆኖም ጳውሎስ በትክክል እያለ ያለውን ለማስተዋል ከጥቅሶቹ ጋር ያለውን የሰፋውን አውድ ልንመለከት ይገባናል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች ሙሉ ምንባብ ሮሜ 3፡31፤ 6፡15፤ 7፡7-12 እና ገላ. 3፡21 ትኩረት በመስጠት እንመርምራቸው፡፡ እነዚህ ጥቅሶ እንዲሁም ሙሉ አውዱ ጳውሎስ ስለህጉ የያዘውን አቋም ለመረዳት እንዴት ይረዱናል?
————————————————————————————
————————————————————————————

የቅድስና በእምነት (Justification by faith) ጽንሰ ሀሳብን ላላስተዋሉ ጳውሎስ ከራሱ ጋር እየተጋጨ ይመስላል፡፡ ክርሰትያን ከህጉ በታች አይደለም ባለበት አፍ ያው ክርሰትያን ህጉን መጠበቅ አለበት ይላል፡፡ ችግሩ የሚፈታው እግዚአብሔር ቅዱስና የሚጠብቀው ከእርሱ ጋር ግንኙነት ከጀመሩ ሰዎች መሆኑን ስናስተውስ ነው፡፡ የቅድስና መለኪያ ህጉ ነው፡፡ ሆኖም ሰዎች በህጉ ሲለኩ እንደማያሟሉና በህጉ በደለኞች ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ህጉ የመዳኛ መንገድ ቢሆን ኖሮ ማንም የዘላለም ህይወት ተስፋ አይኖረውም ነበር፡፡

የክርስቲያን ተስፋ በህጉ ሳይሆን ብቻውን ህጉን በታዘዘውና አማኙን በእርሱ ተአምረኛ ሃይል የእርሱን ፅድቅ እንዲካፈል በፈቀደው (ሮሜ 8፡3፤4) በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ክርስቲያኑ አሁን የእግዚብሔርን ህግ በነፃ ህሊና ሊያገለግል ይችላል ምክንያቱም ክርስቶስ የህጉን ኩነኔ ስለ ወሰደለት ነው) ሮሜ 7፡25-8፤2) በክርስቶስ የመጣው ፀጋ ከህጉ ነፃ የሚያወጣ ሳይሆን ህጉን እንድንታዘዝ የሚያስገድደን ነው፡፡

 ሰኞ    ሰኔ 2 2006 ዓ.ም

ጴጥሮስና ህጉ (1ኛ ጴጥ. 2፡9)

ጴጥሮስ ለኢየሱስ ቅርብ ከነበሩበት ሐዋርያት አንዱ ነበር፡፡ በመጀመርያ ከተመረጡት ውሰጥ ጴጥሮስ በኢየሱስ አገልግሎት ዋና በሚባሉት ክስተቶች በብዙዎቹ ተገኝቷል፡፡ በፊልጵስዮስ ቄሳርያ ኢየሱስ መሲህ እንደሆነ ያወጀው ጴጥሮስ ነበር፡፡ እንዲሁም ኢየሱስ በታሰረበትና በተፈረደበት ሌሊት ወደ ቀያፋ ሲወስዱት ጴጥሮስ አዳኙን ተከትሎ ነበር፡፡ ኢየሱስ በተነሳበት ጠዋት በባህር ዳር ለደቀመዛሙርቱ በተገለፀበት ጊዜ ስለ ክርስቶስ አገልግሎት የተለየ መመሪያን የተቀበለው ጴጥሮስ ነበር፡፡ ህጉ በሆነ ሁኔታ ተቀይሮ ከነበረ ጴጥሮስ ሊያውቅ ይገባ ነበር፡፡

በሐዋ. ስራ 10፡9-14 ጴጥሮስ ኢየሱስ ካረገ በኋላ ለአይሁድ ህግ የነበረውን ጥብቅ አመለካከት በምን መልኩ ይነግረናል ?
————————————————————————————
————————————————————————————

ኢየሱስ ካረገ ከብዙ አመታት በኋላ ነው ጴጥሮስ ራዕዩን የተቀበለው በደቀመዛሙርቱ ስብከት በሺህ የሚቆጠሩ አይሁዳውያን ኢየሱስን እንደ መሲህ ተቀብለዋል፡፡
በክርስቲያን መልዕክት ውስጥ ህጉን የሚያስወግዱ መመሪያዎች መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኙም፡፡ ጠንከር ባለ መልኩ በሐዋርያት ሥራ 10 የተከሰተው ነገር የቀድሞዎቹ ክርስቲያኖች ከአይሁዳዊ ስር መሰረታቸው ጋር እንደነበሩ በግልፅ ይናገራሉ፡፡

1ኛጴጥ. 2፡9ንና ዘፀዓት 19፡6ን ያነፃፅሩ፡፡ የዘፀዓት 19፡6 አውድ (context) ምንድነው?
————————————————————————————
————————————————————————————

ጴጥሮስ አድማጮቹን የንጉስ ካህናት፤ ቅዱስ ህዝብ›› ብሎ ሲጠራ በሲና የህጉን መሰጠት ታሪክ ወዲያው እንዲያስተውሱ ነበር፡፡ እንደ እስራኤል ህዝብ ወራሽ በእግዚአብሔር ህግ ግለጽ በሆኑት የኪዳን ቃላት እንዲመሩ ይጠበቅባቸው ነበር፡፡ ስለዚህ ህዝቡ ያላቸውን ማዕረግ ካስታወሳቸው በኋላ ጴጥሮስ የቅድስና ህይወት እንዲኖሩ ጥሪ አቀረባላቸው (1ጴጥ. 2፡11፤12)፡፡ ከህግ ነፃ የሆነን ወንጌል ከሚያስተምሩ የሀሰት አስተማሪዎች እንዲጠበቁ ያስጠነቅቃቸዋል፡፡ (2ኛ ጴጥ. 2፡21፤ 3፡2)

ጴጥሮስ ህይወቱ ምን ያክል ተመሰቃቅሎ እንደነበር ያስታውሰናል ለእርሱ የተዘረጋለትን ፀጋ ልብ ይበሉ፡፡ እኛስ፡- (1) ያንን አይነት ፀጋ ለሌሎች ማስተላለፍና (2) ህይወታችን ሲበላሽ ያንን ፀጋ ለራሳችን መቀበል የምንችለው እንዴት ነው?

ማክሰኞ             ሰኔ 3 2006 ዓ.ም

ዮሐንስና ህጉ

ለአዲስ ኪዳን ብዙ መጻህፍትን ከማዋጣት (ከማበርከት) አንፃር ዮሐንስ ከጳውሎስ ቀጥሎ ሁለተኛ ነው፡፡ የዮሐንስ ወንጌል፤ ሶስቱን መልዕክቶችና የራዕይን መጽሐፍ የፃፈው ይኽው ዮሐንስ ነው፡፡ እንደ ጴጥሮስ ኢየሱስ በመጀመርያ ከመረጣቸው ደቀመዛሙት አንዱ የነበረና ከኢየሱስ ጋር የተለየ ወዳጅነት የነበረው ነው፡፡ ከኢየሱስ ጋር ከነበረው ቅርበት የተነሳ ብዙ ጊዜ የተወደደው ‹ዮሐንስ›  ተብሎ ይጠራል፡፡ ከወንጌሉ አጨራረስ በመነሳት (ዮሐንስ 21፡25) ዮሐንስ ስለ ኢየሱስ ብዙ የግል መረጃዎችን ያውቅ እንደነበር መናገር ይቻላል፡፡ እንደ ዮሐንስ ለኢየሱስ ቅርብ የሆነው ሰው ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ህግ አስቀርቶ ከሆነ ማወቅ ነበረበት፡፡

ዮሐንስ 15፡1-11 እና ዮሐንስ 2፡3-6ን ያንብቡ፡፡ ከእግዚአብሔር ‹‹ህግጋት›› ጋር አንድ  ሰው ሊኖረው ስለሚገባ ግንኙነት እነዚህ ጥቅሶች ምን ይነግሩናል?
————————————————————————————
————————————————————————————

ወደ ምድራዊ ሕይወቱ ፍፃሜ ሊደርስ ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ ለአባቱ ትእዛዛት ታማኝ እንደሆነ እና በአባቱ ፍቅር ‹‹እንደፀና›› (ዮሐ. 158፡10) ይመሰክር ነበር፡፡ ኢየሱስ ትዕዛዛቱን መወገድ  እንዳለባቸው እንቅፋቶች ሳይሆን ከእርሱ ጋርና ከሌሎች ሰዎች ጋር ላለው ፍቅር መመሪያዎች አድርጐ አያቸው፡፡ የተወደደው ደቀመዝሙር ዩሐንስ ክርስቲያኖች ለእግዚአብሔር ሊያደርጉት ስለሚገባው ነገር ሲናገር ኢየሱስ በወንጌል ውስጥ የሚጠቀምባቸውን የፍቅርና የአንድነትን ተመሳሳይ ቃላት ይጠቀማል፡፡
እንደውም ዩሐንስ የህጉ ማዕከል መሆኑን አስተውሎ ነበር (ለምሳ 2 ዮሀንስ 6) አንድ ሰው ከእግዚብሔርና ከሌሎች ሰዎች ጋር የፍቅር ግንኙነት ከሌለው ህጉን ጠብቄያለሁ ብሎ ሊናገር አይችልም፡፡

‹‹የእግዚአብሔር ህግ ባልንጀሮቻችንን እንደራሳችን እንድንወድ ይጠይቀናል፡፡ ዘኪያም እያንዳንዱ የአዕምሮ ሃይልና ተግባር ወደዚያ አቅጣጫ ማለትም እጅግ መልካም ወደ ማድረግ ሊሰለፍ ይገባዋል፡፡ ሰው የተሰጠውን ልዩ ስጦታ ለሌሎች አምላክን ለማሳየት ሲጠቀምበት እግዚአብሔር ምን ያህል ይደሰት ይሆን! በሰውና በእግዚአብሔር መካከል አገናኝ መስመሮችና የክርስቶስን መንፈስና የሰማይን ባህርይ የሚገልጡ ናቸው፡፡ በጉራ የሚነገረው ሳይሆን የሚታየው የቅድስና ሃይል እጅግ ሃይለኛ ከሆኑት ስብከቶች ይልቅ በግልፅ ይናገራል፡፡ ተራ ቃላት ከሚናገሩት በላይ ስለ እግዚአብሔርና ሰዎችም ማድረግ ሰላለባቸው ነገሮች በኃይል ይናገራል፡፡›› Ellen G. white, manuscript Releases, Vol. 20. P. 138
በህግና በፍቅር መካከል ካለው ግንኙነት አንፃር የርስዎ የግል ልምምድ ምንድነው? ማለትም በግለሰቡ ደረጃ ፍቅር ለእግዚአብሔር ህግ ስለመታዘዝ እንዴት ይገለፃል?

ረቡዕ           ሰኔ 4 2006 ዓ.ም

ያዕቆብና ህጉ

‹‹የተጠራችሁበትን መልካሙን ስም የሚሰድቡ እነርሱ አይደሉምን? ነገር ግን መጽሀፍ ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ እንደሚል የንጉስን ህግ ብትፈጽሙ መልካም ታደርጋላችሁ፤ ለሰው ፊት ግን ብታዳሉ ኃጢአትን ትሰራላችሁ ህግም እንደተላለፊዎች ይወቅሳችኃል፡፡›› (ያዕቆብ 2፡7-9) በአዲስ ኪዳን በያዕቆብ ስም የተፃፈ አንድ መጽሀፍ ብቻ ነው ያለው፡፡ ፀሐፊው የትኛው ያዕቆብ መሆኑን ግልፅ ባያደርግም የኢየሱስ ወንድም የሆነው ያዕቆብ መሆኑን ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡ መጀመርያ ስለየሱስ መሲህነት የተጠራጠረ ቢሆንም (ዮሐ. 7፡5) ያዕቆብ በአዲስ ኪዳን ቤተክርስቲያን ቀስ በቀስ መሪ እስከ መሆን ደርሷል (የሐዋ. 15፡13፤ ገላ. 1፡19)፡፡ በድጋሚ ኢየሱስ መለኮታዊውን ህግ የማስቀረት ሀሳብ ቢኖረው የገዛ ወንድሙ ሊያውቅ ይገባ ነበር፡፡

ያዕቆብ 2፡1-26ን ያንብቡ፡፡ የምዕራፉ መሰረታዊ መልዕክት ምንድነው? ያዕቆብ ህጉን በቁጥር 7-9 እንዳረገው ብቻ ለምን አጠቃለለው? (ከዚያ በኋላ ሁሉንም ህጐች ሰለመጠበቅ ማውራቱ ካልቀረ) እነዚህ ጥቅሶች በፍቅርና የእግዚአብሔርን ህግጋት በመታዘዝ መካከል ያለውን ግንኙነት እንዴት ያሳያሉ?
————————————————————————————
————————————————————————————

ጳውሎስ ስለህጉ ያስተማረውን በስህተት በመረዳት አንዳንዶች ያዕቆብና ጳውሎስ የህጉን ሚና በተመለከተ ይቃረናሉ ብለው ይከራከራሉ፡፡ የክርክሩ ዋና ነጥብ በመዳን ውስጥ ስራ ያለው ቦታ ላይ ነው፡፡ ጳውሎስ ከስራ ውጪ በእምነት በፀጋው መዳናችንን ሲያውጅ (ኤፌ. 2፡8-9) ያዕቆብ ግን ‹‹እምነት ያለ ሥራ ሙት ነው›› (ያዕቆብ 2፡26) የሚለው ነጥብ ላይ ያሰምራል፡፡ እነዚህ አረፍተ ነገሮች አይገጩም፤ ያእቆብ ጳውሎ በተለያዩ ቦታዎች ጻጋ ህጉን እንደማያስወግድ የተናገረው በጠንከራ መንገድ እየገለፀ ነው፡፡ ልክ ጳውሎስ በሮሜ 13፡9) እንዳደረገው ያዕቆብ የእግዚአብሔር ህግ ማዕከል ፍቅር መሆኑን ሙሉ በሙሉ ተረድቷል፡፡ (ያዕ. 2፡8) አንድ ሰው ፍቅርን በተግባር ካላሳየ የእግዚአብሔርን ህግ በእውነት ጠብቄያለሁ ብሎ ሊናገር አይችልም፡፡

ሐሙስ                  ሰኔ 5 2006 ዓ.ም

ይሁዳና ህጉ

በአዲስ ኪዳን ከሚገኙ አጭር መጽሀፎች አንዱ የሆነው ይሁዳ በሌላው የየሱስ ወንድም እንደተፃፈ ይታመናል፡፡ ምንም እንኳን ፀሐፊው ራሱን እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹ባርያ›› ቢቆጥርም የያእቆብ ወንድም መሆኑን ያምናል (ይጠቅሳል)፡፡ ማቴዎስ በወንጌሉ ያዕቆብንና ይሁን ከኢየሱስ አራቱ  ወንደሞች መካከል ሁለቱ መሆናቸውን ስለሚናገር ይህ አጭር ፅሁፍ የአዳኙ ወንድም ይሁዳ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ቀድም ብለን እንዳየናቸው እንደ ሌሎች የመጸሀፍ ቅዱስ ፀሐፊዎች ሁሉ ኢየሱስ ህጉን ሽሮ ከሆነ ይሁዳም ያውቅ ነበር፡፡
ይሁዳ ስለህግ ወይም ትዕዛዛት ጠቅሶ ባይፅፍም ሙሉ ደብዳቤው ለእግዚአብሔር ታማኝ ስለመሆንና ህጉን የመተላለፍን ውጤቶች የያዘ ነው፡፡
ይሁዳ ቁ. 4ን ያንብቡ፡፡ ለውይይታችን ጠቃሚ በሆነ ሁኔታ ምን እየተናገረ ነው ያለው? የፀጋ መጠቀስ የህጉን መኖር ይጠይቃል፤ ምክንያቱም ኃጢአት ባይኖር ኖሮ ፀጋ አያስፈልግም ነበር (ሮሜ 5፡18-6፤15) እነዚህ የሃሰት አስተማሪዎች የሚያሰተምሩት ትምህርት ክፉ ከመሆኑ የተነሳ ይሁዳ ጌታን ከመካድ ጋር እኩል ያደርገዋል፡፡

ዕብራውያን 3፡7-19 በይሁዳ 5-7 ላይ ብርሃንን የሚያብራው እንዴት ነው? እነዚህ ጥቅሶች የመታዘዝንና የእምነትን ግንኙነት እንዴት ያሳዩናል?
————————————————————————————
————————————————————————————

በራሱ ዘዴዎች መንገድ ይሁዳ አድማጮቹን ከግብፅ ባርነት ስለወጡት እስራኤላውያን ልምምድ ያስተውሳቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ብርታቱን አሳይቷቸዋል፤ ህጉንም ሰጥቷቸዋል፤ ታማኝ ሳይሆኑ ሲቀሩ ግን ከእርሱ ከመለየት የመነጨን የከፉ ውጤቶች አሰተናገዱ፡፡ ይሁዳ እንደሚያረጋግጠው ሰዎች ይወድቃሉ፤ የሚወድቁትም ፍርድ (ኩነኔ) ይጠብቃቸዋል፡፡ ይሁዳ እንደሌሎቹ የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍሎች ሃሳቡ ግልጽ ነው፤ እምነት አለኝ የሚሉ ሁሉ እምነታቸውን በታማኝ ህይወት ለመግለፅ ፈቃደኛ ሊሆኑ ይገባል፡፡
የይሁዳን መጽሀፍ ያንብቡ፡፡ ጠንካራ ማስጠንቀቂያዎች ቢኖሩትም ለራስዎ የሚሆኑ ምን አይነት የተስፋ ቃሎቹን ያገኛሉ?

ዓርብ          ሰኔ 6 2006 ዓ.ም

ተጨማሪ ጥናት፡- የEllen G. white ን “The law in the Christian age” የሚለውን ጽሁፍ ከ signs of the times, august 5, 1886 ያንብቡ፡፡

‹‹ሐዋርያት ለምን ለእግዚአብሔር ንስሃ ስለመግባት ያስተምራሉ? ምክንያቱም ሃጢያተኛው ከአብ አባት ጋር ችግር ውስጥ ስላለ ነው፡፡ ህጉን ተላልፏል፤ ኃጢአቱን አይቶ ንስሀ መግባት አለበት፡፡ ቀጣዩ ስራው ምንድነው? ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻ ደም ወዳለው ወደ ኢየሱስ መመልከት አለበት፡፡
በክርስቶስ ማመን አስፈላጊ ነው ምክንያቱም በህጉ ውስጥ የማዳን ብቃት ስለሌለ፡፡ ህግ ይኮንናል እንጂ ተላላፊውን ይቅር ሊል አይችልም፡፡ ኃጢአተኛው በክርስቶስ ደም ብቁነት ብቻ መተማመን አለበት፡፡ መሃሪው አዳኝ ‹‹ከእኔ ጋር ሰላም እንዲሆን የእኔን ብርታት ይውሰድ ከዚያም ከእኔ ጋር ሰላምን ያወርዳ (ይታረቃል)›› ይላል ጌታችን እንደተናገረው ብዙ ይቅር የተባለ ብዙ ይወዳል፤ እንዲሁም ራሱን በትክክል የሚያይ የእግዚብሔርን ቅዱስ ህግ ተላላፊና በኃጢአት የተጨማለቀ መሆኑን የሚያውቅ ይቅርታ እንደሚያስፈልገው እሱ ብቻ ይሰማዋል፡፡ በተቀደሰው ህግ ላይ ሙሉ መታመን ያለው ሰው የራሱን የበዙ ውድቀቶች በግልጽ ተመልክቶ በእርግጥም ብዙ ይቅር  እንደተባለ ይሰማዋል፡፡›› Ellen G. white, signs of the times, August 5, 1886

የመወያያ ጥያቄዎች፡-

  1.  ከላይ የተቀመጠውን የኤለን ጂ. ኋይት ንግግር በጥንቃቄ ያንብቡ፡፡ በዚህ ሩብ አመት በተገለፁት መጽሀፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮዎች ላይ ይህ ጽሁፍ ብርሃን የሚያበራው እንዴት ነው ?
  2.  በይሁዳ ቁ. 4 ላይ የተሰጠውን ማስጠንቀቂያ የበለጠ ይመርምሩ፡፡ ሰዎቹ የእግዚአብሔርን ፀጋ እያወጁ ከሆነ በግልጽ እንደሚታየው እነርሱ አማኞች ናቸው፡፡  ሆኖም ይሁዳ ጌታን እየካዱ እንደሆኑ ይናገራል፡፡ የእግዚአብሔር ፀጋ ህጉን ሽሯል ለሚሉ ይህ ምን አይነት ጠንካራ መልእክትን ያስተላልፋል? ሰዎች ህጉ ተፈፅሟል ብለው ሲያስወግዱት በእርግጥም እያስወገዱ ያሉት ምንድነው? 
  3. ህጉን መካድ ወይም አንዲቱን ትዕዛዝ ብቻ መተው የእግዚአብሔርን ህግ መገልበጥ ፍላጐቱ ለሆነው ለሰይጣን የሚጠቅመው እንዴት ነው?

Copyright © 2013 Ethio SDA . All Rights Reserved